Free Essay

Technology and Its Impact

In: Social Issues

Submitted By yona
Words 2260
Pages 10
:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com «ዲጂታል ዲጂታል» «ዲጂታላይዜሽን1» እና «ዲጂታል» ሌቦች
ከመቀሌ ከተማ የሃያ ደቂቃ መንገድ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው የአቡነ ያሳይ ገዳም አንድ ፈረንጅ ይመጣል፡፡ ሰውዬው የመጣው ብቻውን ሳይሆን ከአንዳንድ ባለ ሥልጣናት ጋር ነበር፡፡ እነዚያ ባለ ሥልጣናት የገዳሙን ሰዎች ጠርተው «ይኼ ፈረንጅ በገዳሙ ያሉ ትን ጽሑፎች በሙሉ በዲጂታል ፎቶ ግራፍ እንዲያነሣ ይፈቀድለት» ብለው መመርያ ይሰጣሉ፡፡እርሱም በሙሉ በዲጂታል ካሜራ ያነሣቸዋል፡፡ » እኛ ወደ ገዳሙ ለጥናት በሄድን ጊዜ «ከእናንተ በፊት አንድ ፈረንጅ መጥቶ መጻሕፍቱን ሁሉ በካሜራ አነሣ» ይሉናል፡፡ ገዳማውያኑ ፈረንጁ ፎቶ ማንሣቱን እንጂ፣ ለምን እንዳነሣ፣ አንሥቶ የት እንደ ሚወስደው፣ ባለቤትነቱ የማን እንደሆነ አልተነገራቸውም፤ እነርሱም የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ብቻ በሙዳየ ምጽዋቱ ውስጥ 1970 ብር መጨ መሩን በምስጋና ያስታውሱታል፡፡ እነዚህ ገዳማውያን ይህንን ቅርስ ጠብቀው ለዘመናት የኖሩ ናቸው፡፡ የጥበቡ የባለቤትነት መብት (Intellectual property right) አላቸው፡፡ በእነዚያ ቅርሶች መጀመርያ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው እነርሱ ነበሩ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ደግሞ ይህ ፈረንጅ የእነርሱን የሺ ዓመታት ጽሑፎች ቅጅ እየወሰደ መሆኑን ሊነገራቸው ይገባ ነበር፡፡
1

ዲጂታላይዜሽን የሚለውን ቃል እንዳለ በእንግሊዝኛው የወሰድኩት እርሱን ወደ አማርኛ ሊመልስ የሚችል ቃል አጥቼ ነው፡፡ ያማከርኳቸውም ጥቂት ቀናት ለምነውኛል፡፡ ምናልባት እግዜር ቢፈቅድ ተባብረን እናገኝለታለን፡፡

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
ይህንን ታሪክ በቁጭት የተናገሩት በኢትዮጵያ ጥንታዊ ጽሑፎች ላይ ጥናት በማድረግ እና በመጻፍ የታወቁት ዶክተር አየለ በከሪ ናቸው፡፡ «የጥንታዊ ጽሑፎች አያያዝ እና አጠባበቅ በኢትዮጵያ» በሚል ርእስ የካቲት 29 ቀን 2004 ዓም የብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት እና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ ባዘጋጀው ዐውደ ጥናት ላይ፡፡ ኢትዮጵያ ጥንታውያን መዛግብት ከሚገኙባቸው ጥቂት የዓለም ሀገሮች አንዷ ናት፡፡ ዐጽማቸውን ያለምልም፣ ነፍሳቸውንም ይቀበልና አባቶቻችን ዕውቀት ፈላጊዎች፣ ጥበብ አሳሾች በመሆናቸው ከእንግሊዝ እስከ ሕንድ ከግብጽ እስከ ሩሲያ እያሰሱ የዓለሙን ዕውቀት ወደ ሀገራችን አምጥተውልናል፡፡ ብሉይ ከሐዲስ ከነ ሊቃውንቱ ሳይጎድልብን፤ የግሪኮቹን ፈላስፎች የነ አሪስቶትልን እና ሶቅራጥስን፣ ብሎም የነ ፕሉቶን ፍልስፍና በአንጋረ ፈላስፋ፤ የሕንዶቹን ትምህርት እና የሥነ ምግባር እሴት በመጽሐፈ በርለዓም ያገኘነው በዚህ የተነሣ ነው፡፡ እነርሱም ራሳቸው በዘመናቸው የደረሱበትን በብዕራቸው እና በሥዕላቸው አሥፍረው ልናል፡፡ ዛሬ አሉ የሚባሉት ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ ጥንታውያን የግእዝ መጻሕፍት የእነዚሁ አባቶቻችን የድካም ፈሬዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ጥንታውያን የዕውቀት ክምችቶች የመዝረፍ እና ከሀገራቸው የማሰደድ ተግባር የተጀመረው ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ መሆኑን የሚናገሩ አሉ፡፡ በልዩ ልዩ ምክንያት ወደ ሀገሪቱ የመጡ አሳሾች፣ ሚሲዮናውያን፣ የዲፕሎማሲ ሰዎች፣ ነጋድያን እና ተመራማሪዎች እነዚህን የጽሑፍ ቅርሶች እየጫኑ

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
ሲያጓጉዙ ኖረዋል፡፡ እንደነ ጄምስ ብሩስ ያሉት አሳሾች እስከ ሦስት ሺ የሚጠጉ መጻሕፍትን ማውጣ ታቸው ይነገራል፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ አምባ ላይ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት እና ቤተ መዛግብት የመገንባት ዓላማ ስለነበራቸው አብዛኞቹ በጎንደር አድባራት እና አብያተ መንግሥታት የነበሩትን የጽሑፍ ቅርሶች ወደ መቅደላ አምባ አጓጉዘው አከማችተዋቸው ነበር፡፡ መቅደላ አምባ ተሠብሮ ዐፄ ቴዎድሮስ በጀግንነት ራሳቸውን ሲሠው እንግሊዞች የመቅደላን ቅርሶች ዘርፈው ወስደዋቸዋል፡፡ በቅርቡ በተሰጡ ግምቶች ወደ 2 ቢሊዮን ፓውንድ የሚገመት ንብረት ከመቅደላ መዘረፉ ይነገራል፡፡ ከዚያም በኋላ ቢሆን ዝርፊያው አላቋረጠም፡፡ የኢትዮጵያ ቅርሶች ከጃፓን እስከ አሜሪካ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ኖርዌይ ተበትነዋል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ይህንኑ ጉዳይ ሲገልጡት «የኢትዮጵያ መጻሕፍት እንደ ጭሮ ያልተዘሩበት፣ እንደ እሥራኤል ዘር ያልተበተኑበት ቦታ የለም» ማለታቸው ይወሳል፡፡ አሁን ዘመኑ በጥንታውያን ቅርሶች ላይ ጠበቅ ያለ ርምጃ የሚወሰድበት እየሆነ ሲመጣ፤ በሌላ በኩልም ታላላቅ መጻሕፍትን በጠረጲዛ ላይ ከማንበብ ይልቅ ቀላል ቅጃቸውን (soft copy)ማንበብ እየተዘወተረ ሲሄድ፡፡ አንድን የብራና መጽሐፍ ለመስረቅ፣ለማሰረቅ እና ለማጓጓዝ የሚወስደው ጊዜ እና ወጭ እየከበደ ሲመጣ የሌብነት ዓይነቱ ተቀየረ፡፡

ዲጂታል ዲጂታል ሌቦች

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
«ዲጂታላይዜሽን» ጥንታውያን ጽሑፎችን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱ፣ በየጊዜው ለአገልግሎት መጠቀሙ እና በየወቅቱም እነርሱን ፎቶ ማንሣቱ ታሪካዊ ውርጅናሌያቸውን እያጠፋው በመምጣቱ የተፈጠረ ዘዴ ነው፡፡ «ዲጂታላይዜሽን» የጽሑፍ ሥራዎቹን በዲጂታል ካሜራዎች በማንሳት በኮምፒውተር በኩል በተለይም በመሥመር ላይ (on line) ለአንባብያን እና ለተመራማሪዎች የማቅረብ ዘዴም ነው፡፡ በዐውደ ጥናቱ ላይ ተሳትፈው የነበሩ እንደ እና ዶክተር ባሕሩ ዘውዴ ዓይነት ምሁራን «ዲጂታላይዜሽን ቅርሶቹን እንዳይነቃነቁ ለመጠበቅ፣ በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እና የቦታ ጥበትን ችግርን ለመፍታት» ጠቀሜታ እንዳለው ገልጠው ነበር፡፡ «በተለይም አብዛኞቹ የሀገራችን የጽሑፍ ሀብቶች የሚገኙባቸው የእምነት ቦታዎች ከሕዝቡ መኖርያ የራቁ በመሆኑ ለተመራማሪዎች እና ለተማሪዎች የመደረስ ችግር አለባቸው፡፡ ጽሑፎቹን በዲጂታል ቅጅ ማስቀመጥ ይህንን ችግር ይፈታል» ብለዋል፡፡ «ይህ የሚሆነው ግን» አሉ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ «ጣምራ እንቅስቃሴ ሲኖረን ነው»፡፡ እርሳቸው ጣምራ እንቅስቃሴ ሲሉ የገለጡት የባለቤትነትን መብት ከዲጂታላይዜሽን ጋር የማጣመርን ሂደት ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ለጥቅም የተፈጠረ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ነገር ግን የሂደቱ ባለቤቶች እኛው ራሳችን ሆነን ማን ዲጂታላይዝ ያደርጋል፣ እንዴት? ማን ይፈቅዳል? ባለቤቱ ማነው? የባለቤቱ ተጠቃሚነትስ ምንድን ነው? ቅጅው የት የት ይቀመጣል? የሚሉትን ካልወሰንን በቀር ለዝርፊያ የሚያጋልጠን ነው» ብለዋል፡፡

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
በአሁኑ ጊዜ አያሌ ፈረንጆች እና የፈረነጁ2 አበሾች በዲጂታል ስርቆት ላይ ተሠማርተው በሀገሪቱ ጥንታውያን ቦታዎች ላይ ላይ ታች በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ስርቆት ላይ የተሠማሩት አካላት ሦስት ዓይነት ናቸው፡፡ 1. በጥናት እና ምርምር ስም ወደ ሀገር የሚገቡ ፈረንጆች፡፡ እነዚህ ሰዎች ጥናት እና ምርምር እናደርጋለን፣ ጥንታዊ ጽሑፎችን ዲጂታላይዝ እናደርጋለን እያሉ ወደ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ የሚመጡ ናቸው፡፡ ከመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች እና ከእምነት ተቋማት ፈቃድ አግኝተው በየታሪካዊ ቦታዎች በመዘዋወር መጻሕፍቱን እና መዛግብቱን ፎቶ የሚያነሡ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት ስርቆታቸው የተሳካ እንዲሆን ያደረጉላቸው ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ ሀ/ አመለካከት፡፡ ፈረንጅ ሁሉ የተማረ፣ ደግ፣ ሥልጡን እና ቅን ነው ብሎ የማሰብ ችግር በሕዝባችንም ሆነ በተቋሞቻችን ዘንድ አለ፡፡ እናንተ ሐበሻ በመሆናችሁ ስትፈተሹ ፈረንጅ የማይፈተሽባቸው፤ ከእናንተ ከሀገሬው ሰዎች ይልቅ ፈረንጅ ቅድሚያ የሚያገኝባቸው አያሌ አጋጣሚዎች ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ እንዲያውም አንድ የስብሰባው ተሳታፊ በዚህ ጉዳይ የገጠመውን ነገር ነግሮን ነበር፡፡ «እኔ እና አንዲት ፈረንጅ ወደ አንዲት ገዳም አንድ ዓይነት ደብዳቤ ይዘን ሄድን፡፡ የገዳሙ ሰዎች ለእኔ አንዲት መጽሐፍ ብቻ እንድመለከት ሲፈቅዱልኝ እርሷን ግን ፈረንጅ በመሆኗ ብቻ ሁሉንም መጻሕፍት በፎቶ ግራፍ እንድታነሣ ፈቀዱላት፡፡ በወቅቱ ተናድጄ ምክንያቱን ስጠይቃቸው እርሷኮ ፈረንጅ ናት ነው ያሉኝ፡፡»
«መፈርነጅ» ማለት፡ ሁሉን ነገር ለፈረንጅ መስጠት፣ ደግ ፈረንጅ ብቻ ነው ብሎ ማሰብ፤ ለፈረንጅ ልዩ ትኩረት መስጠት፣ መፈርነጅ» ፈረንጅን መከተል፣ ፈረንጅን ብቻ ማድነቅ፣ ለፈረንጅ ሁሉን ክፍት ማድረግ፣ ማለት ነው፡፡
2

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
በአንድ ወቅት በአፋር ክልል የአንትሮፖሎጂ ጥናት ያደረገ ኢትዮጵያዊ ፈረንጅ በመሆናቸው ብቻ የርሱን የጥናት ክልል ለውጭ ሰዎች እንደተሰጠበት በምሬት ሲናገር ሰምቼው ነበር፡፡ ለ/ ሁለተኛው ችግር ደግሞ ነገሮችን ከጊዜያዊ ጥቅም አንፃር የመመዘን ችግር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ሀብት እየዘረፉ መሆኑን ፈቃጆችም ሆኑ ቅርሱን የያዙት አካላት አልተረዱትም፡፡ በዚህም የተነሣ በሙዳየ ምጽዋት የሚያስገቡዋቸውን ጥቂት ሺ ብሮች እንደ ትልቅ ርዳታ በማየት ዝርፊያውን ይፈቅዱላቸዋል፡፡ የሚተባበሯቸው አካላትም የውሎ አበል ገንዘብ ማግኘታቸውን፣ ከፈረንጅ ጋር መዋላቸውን፣ ጥቃቅን መሣርያዎችን መረዳታቸውን እንጂ ሀገር መሸጣቸውን አልተረዱም፡፡ 2. መንግሥታዊ አካላት፡- ምንም ዓይነት በቂ የሕግ ማዕቀፍ በሌለበት ለእነዚህ ፈረንጆች ፈቃድ በመስጠት በሕግ ሽፋን የሀገር ሀብት እንዲዘረፉ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ጥንታዊ ጽሑፎችን ወደ ዲጂታል ስለ መቀየር የወጣ የአሠራር መመርያም ሆነ ሕግ እንደሌለ በዐውደ ጥናቱ ላይ ሲገለጥ ነበር፡፡ በርግጥ አንድ የዲጂታል የደረጃ መመርያ እየወጣ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ስርቆቱ ግን ከሕጉ ቀድሞ እየተፋጠነ ነው፡፡ ምናልባትም ሕጉ ሀብቶቹ ሁሉ ካለቁ በኋላ ሊወጣም ይችላል፡፡ በእነዚህ አካላት ዘንድ የግንዛቤ እጥረት ያለ ይመስላል፡፡ በአካል የሚታየውን የብራና መጽሐፍ መውሰድን እንጂ የብራናውን መጽሐፍ ፎቶ ግራፍ ማንሣትን እንደ ስርቆት አያዩትም፡፡ አንድ ቱሪስት የሚሠራው ሥራ አድርገው ነው የሚገምቱት፡፡ «ተባበሯቸው» ብለው በሁለት መሥመር የሚጽፏት ደብዳቤ «ሀገሪቱን ይዘርፉ ዘንድ ተባበሯቸው» ማለታቸው መሆኑን ስንቶቹ ይሆን የተረዱት?

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
አንዳንድ በዲጂታል ሥራው ላይ የተሠማሩ ኅሊና ያላቸው ሰዎች መጻሕፍቱን ካነሡ በኋላ ለመንግሥታዊ እና ሃይማኖታዊ አካላት ስስ ቅጅውን (soft copy) በሚሰጡበት ጊዜ የፍላሹን ማነስ በማየት ኃላፊዎቹ መሳቢያቸው ውስጥ አስቀምጠውት እንደሚቀሩ ያጋጠማቸውን የገለጡ ሰዎችም ነበሩ፡፡ ተባባሪ አካላት፡- በቤተ ክህነት፣ በእስልምና ጉዳዮች፣ በአስጎብኚ ድርጅቶች፣ በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቦች አካባቢ የሚገኙ፣ ኅሊናቸውን ለጥቅም የሸጡ ግለሰቦች ሥልጣናቸውን እና መብታቸውን በመጠቀም ይህ የሀገር ሀብት እንዲዘረፍ እያደረጉ ነው፡፡ ባለፈው ሰሞን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚሳደብ እና የሚያቃልል ፊልም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት እንዲሠራ የፈቀዱት የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት መሆናቸውን ማስታወሱ ብቻ የእምነት ተቋማት ለፈረንጆች ለሚጽፏቸው ደብዳቤዎች ጥንቃቄ እንደማያደርጉ ማሳያ ይሆናል፡፡ ያንን ፊልም አንድ አበሻ የሚሠራው ቢሆን ኖሮ መጀመርያ ነገር አይፈቀድለትም ነበር፡፡ ቢፈቀድ ለትም እጅግ አሰልቺ ደጅ ጥናት ያስፈልገው ነበር፡፡ የመፈርነጅ አመለካከት የቤተ እምነት መሪዎች አንዱ ችግር ነው፡፡ ስለዚሀም አያሌ የፈረንጅ ዲጂታል ሌቦች ከየቤተ እምነቱ ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን የቤተ እምነቶችን «የትብብር ደብዳቤ» እየያዙ በየገዳማቱ እና አድባራቱ፣ በየመስጊዶቹ እና የመድረሳ ቤቶቹ ካሜራዎቻቸውን አንግተው ሲዘርፉ ይውላሉ፡፡ ከፈረንጅ ጋር መዋል፣ ማውራት፣ መታየት እና ፎቶ መነሣትን እንደ ሊቅነት የሚቆጥሩ፣ ከሊቃውንት ጋር ከመዋል ይልቅ ከፈረንጅ ጋር ሲውሉ ምሥጢር የተገለጠላቸው የሚመስላቸው አያሌ የየቤተ እምነቱ

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
«ፊደል ቆጣሪዎች» እና «እንጀራ ፈላጊዎች» ፈረንጆችን ይዘው በየገዳማቱ ሲዞሩ ታገኟቸዋላችሁ፡፡ ብርቱዎቹ መነኮሳት እና ካህናት፣ ጠንካሮቹ ገዳማውያን ቅርሳችንን አናስነካም ሲሉ በሥልጣናቸው እያስ ፈራሩ አንድ ሊቅ እንዳሉት «የሺ ዓመትን ሀብት በአንድ ፍላሽ የሚያስወስዱ» እነርሱ ናቸው፡፡ ዲጂታል ሌቦች በሀገሪቱ ላይ ሦስት አደጋዎች እያደረሱ ነው፡፡ 1/ የመጀመርያው የእነርሱ ባልሆነው ቅርስ እያጋበሱት ያለው ትርፍ ነው፡፡ ባልጻፉት፣ ባልጠበቁት እና መሥዋዕትነት ባልከፈሉበት ቅርስ ፈረንጅ ሆነው ካሜራ ስላላቸው ብቻ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ገበያዎች የሀገሪቱን የጽሑፍ ቅርሶች በዲጂታል እየቸበቸቡ ናቸው፡፡ ይህንን በቀላሉ ለማየት e bay የተሰኘው የመሥመር ላይ የቅርሶች መሸጫ ድረ ገጽን መጎብኘት ይበቃል፡፡ እዚያ ቦታ የኢትዮጵያ ጥንታውያን ሥዕሎች እና ጽሑፎች ያለ ባለቤቶቹ ፈቃድ እየተቸበቸቡ ናቸው፡፡ 2/ ሁለተኛው ደግሞ የባለቤትነት መብቱን መውሰዳቸው ነው፡፡ እነዚሀን ቅርሶች ለማዘጋጀት፣ ለመጠበቅ እና ከአደጋ ለመታደግ የሕይወት ዋጋ የከፈሉት ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ የአእምሮም ይሁን የንብረት ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ገዳማት እና አድባራት፣ ሊቃውንት እና መምህራን ነው፡፡ ዲጂታል ሌቦች ግን ቅርሱን ብቻ ሳይሆን ባለቤትነቱንም ዘርፈውታል፡፡ የሚያያዙበትም፣ የሚያባዙትም፣ ቅጅ የሚሰጡትም እነርሱ ናቸው፡፡ በዚህም የቅጅ መብቱ (Royal payment) የባለቤቶቹ የኢትዮጵያውያን ሳይሆን ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር የቆረጡት የዲጂታል ሌቦች ሆኗል፡፡

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
አንዳንድ ምሁራን እንዳስረዱት ሌላው ቀርቶ ዲጂታል ሌቦቹን መዛግብቱ እና መጻሕፍቱ ፎቶ ለተነሣ ባቸው አካላት እንኳን ቅጅዎቻቸውን እንዲሰጡ የሚያስገድዳቸው ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡ ለምሳሌ የትግራይን ገዳማት መዛግብት እና መጻሕፍት በዲጂታል ካሜራ የሰበሰበ አንድ ፈረንጅ አለ፡፡ እስካሁን ግን ለገዳማቱም ሆነ ለመንግሥታዊ አካላት ቅጅ አለመስጠቱን የገለጡ ነበሩ፡፡ ይህንን ጉዳይ ዶክተር አየለ በከሪ በጤፍ ምሳሌነት ነበር ያስረዱት፡፡ ጤፍ ለብዙ ሺ ዓመታት የበቀለው፣ ጥቅም ላይ የዋለው እና ለዓለም የተበረከተው በኢትዮጵያ ከኢት ዮጵያ ነው፡፡ ሆላንዶች በምርምር ስም ወስደው የጤፍን የተጠቃሚነት መብት (patent right) አወጡ፡፡

አሁን የጤፍ ዓለም ዐቀፍ ተጠቃሚዎች ሆላንዶች እንጂ ባለቤቶቹ ኢትዮጵያውያን አልሆኑም፡፡ በጥንታውያን የጽሑፍ ሀብቶቻችንም ላይ የሆነው እንደዚሁ ነው፡፡ 3/ እነዚህ በምርምር ስም የሚነቃነቁ አካላት እንዴት ዲጂታላይዝ ማድረግ እንዳለባቸው የወጣ ሕግም ሆነ የአሠራር ደረጃ ባለመኖሩ መዛግብቱን እና ጽሑፎቹን ለእነርሱ በሚያመቻቸው መንገድ እያገላበጡ ያነሷቸዋል፡፡ ለጽሑፎቹ ደኅንነት እና ጥንቃቄ አይጨነቁም፡፡ በመተሻሸት፣ በመላላጥ እና በመገላበጥ ለሚደርስባቸው አደጋ ተጠያቂ አይሆኑም፡፡ ይህ ደግሞ እነርሱ ቅርሱን ሲዘርፉ እኛ ግን የቅርሱ የነጡ ድኾች እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የመጡት ዶክተር አሕመድ ሐሰን «ቆዳን እድሜህ ስንት ነው ቢሉት ቅቤን ጠይቁት አለ» ብለው ተርተው ነበር፡፡ ቆዳ ይህንን ያለው

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
የቆዳን እድሜ የሚያስረዝመው በቅቤ መታሸቱ ስለሆነ ነው፡፡ አሁንም የእነዚህ ጥንታውያን የጽሑፍ ሀብቶቻችን እድሜ ማጠሩ እና መርዘሙ በእኛ ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ ገልጠውት ነበር፡፡

ይደረግ? ምን ይደረግ?
ዲጂታላይዜሽን ጥንታውያን መዛግብትን እና ጽሑፎችን ለመጠበቂያ፣ ለመጠቀሚያ እና ከአደጋ ለመከላከያ ከሚውሉ ዘመናውያን ዘዴዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ግን በሠለጠነ ባለሞያ፣ በተቀላጠፈ እና በተጠናከረ አሠራር፣ እና ተገቢ በሆነ ሕግ ሲመራ ብቻ ነው፡፡ ያለበለዚያ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል፡፡ እናም ይህንን ችግር ለመከላከል በወቅቱ የነበሩ ባለሞያዎች እና መንግሥታዊ አካላት የሚከተሉትን መፍትሔዎች ጠቁመው ነበር፡፡

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
• • ማኅበረሰቡ ስለ ዲጂታላይዜሽንን ጥቅም እና ጉዳት የሚያውቅበትን መንገድ መፈለግ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የእምነት ተቋማት፣ የባህል ቢሮዎች፣ የቅርስ መሥሪያ ቤቶች፣ አስጉብ ኚዎች፣ የጉምሩክ ባለሞያዎች፣ የፖሊስ እና ወታደራዊ አካላት፣ የገዳማት እና አድባራት፣ የመስጊዶች እና መድረሳ ቤቶች ኃላፊዎች፣ አባቶች እንዲያደርጉ ማስተማር • የፈቃድ ሰጭ የመሥሪያ ቤቶች አሠራር የደዲጂታል ተጠቃሚነትን እንጂ ስርቆትን በማያበረ ታታበት መንገድ እንዲቃኝ ማድረግ • የጥንታዊ ጽሑፎችን ዲጂታላይዜሽን በተመለከተ ራሱን የቻለ ሕግ ማውጣት፡፡ በሕጉም ለማን ይፈቀዳል? ማን ይፈቅዳል? በምን ዓይነት ሁኔታ? የባለቤትነት መብት፣ የቅጅ መብት፣ ቅጅ የማግኘት አሠራር፣ በምን ዓይነት ጽሑፎች ላይ ይፈቀዳል፣ የአሠራር ደረጃው ምን መሆን አለበት? ከሀገር ከወጡ በኋላ ያለውን ክትትል፣ የሚመለከቱ ጉዳዮች እንዲካተቱ ቢደረግ • ቢያንስ ሕግ እስኪወጣ ድረስ አሁን በየቦታው ተሠማርተው መጻሕፍቱን እና መዛግብቱን ፎቶ እያነሡ ያሉትን አካላት ማቀብ ቢቻል • በደቡብ አፍሪካ ማሊዎች በቲምቡክቱ አካባቢ እንዳደረጉት እኛም የራሳችን የዲጂታላይዜሽን ማዕከል በሀገራችን ብንከፍት ሥራውን በራሳችን ሰዎች እኛው ለመሥራት የምንችልበት መንገድ ይፈጠር ነበር፡፡ በርግጥ በዚህ ላይ ሁለት ችግሮች መከሰታቸውን አጥኚዎቹ ተናግረው ነበር፡፡ እና መምህራን ስለ ጉዳዩ ዐውቀው ጥንቃቄ

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
የመጀመርያው እኤአ በ2010 ታኅሣሥ ወር ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ተደርጎ የነበረው የአፍሪካ የጥንታውያን ጽሑፎች ጉባኤ የምሥራቅ አፍሪካ የዲጂታላይዜሽን ማዕከል በአዲስ አበባ እንዲቋቋም ወስኖ እና ድጋፍ ለማድረገም ቃል ተገብቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች መተከል ያለበት እኔ ጋ ነው እያሉ ሲከራከሩ ሁለት ዓመት አለፈ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ተተከለ፣ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት እና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ ግቢ ሁሉም ያው አዲስ አበባ ነበረ፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራዊ ራእይ አጥተን ሌሎች ዕድሉን እንዳይወስዱት ያሰጋል፡፡ ቀማኛ ሲጣላ ተስማምቶ እንዳይበላ መንትፋቸው ሄደች ዘዴኛ ቡችላ ይል ነበር «ተረት በሥዕል» የተሰኘው የልጆች መጽሐፍ፡፡ ሁለተኛው ችግር ደግሞ ሥራዎችን ሁሉ በውጭ ድጋፍ ብቻ የማሰብ የመፈርነጅ ችግር ነው፡፡ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ዩኔስኮ፣ ዩኤስ አይዲ ካልገቡበት ገባሬ ሠናይ ቄስ እንደጠፋበት ቅዳሴ ሥራው ይተጓጎላል ብሎ የመስነፍ አመለካከት አለ፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህን የመሰለውን ከታሪካቸው፣ እምነታቸው እና ማንነታቸው ጋር የተሣሠረ ተግባር ለማከናውን ግልጽ፣ ከዘረኛነት እና ፖለቲካዊ ወገንተኛነት የጸዳ አሠራር እስከተዘረጋ ድረስ ሕይወታቸውን ጭምር የሚሰጡ መሆናቸው የተረሳ ይመስላል፡፡

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
• በገዳማት እና አድባራት ርዳታ እና ሥራ ላይ የተሠማሩ አያሌ ማኅበራት በኢትዮጵያ አሉ፡፡ እነዚህ ማኅበራት መዛግብቱ እና መጻሕፍቱ ለሚገኙባቸው ቦታዎች ቀረቤታ አላቸው፡፡ በመሆኑም ግንዛቤው እንዲኖራቸው ቢደረግ በሚጓዙበት ቦታ ሁሉ ዕውቀቱን የማስፋፋት ዕድል ይኖራቸው ነበር፡፡ • በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ የሞቱ መዛግብት(dead files) ተብለው3 የተወረወሩ ነገር ግን የሀገሪቱን ታሪክ የያዙ ጽሑፎች፣ ደብዳቤዎች እና መዛግብት ወደ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት እና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ እንዲላኩ ቢደረግ በአጠቃላይ ዘመናዊነት ዘመናዊ አኗኗርን ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ ስርቆትንም አምጥቷል፡፡ ይህ ዘመናዊ ስርቆት ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ ያለ ጥንታዊ ሀብት እና መሠረት የሚያስቀር ነው፡፡ አውሮፓውያን በ16ኛ እና 17ኛ ክፍለ ዘመን የሕዳሴውን መንገድ ሲጀምሩ ወደ ጥንታውያን ዕውቀቶቻቸው፣ ትምህርቶቻቸው እና አስተሳሰቦቻቸው በመሄድ አስቀድመው እነዚያን ነበር የመረመሩት፡፡ የጠፉባቸውንም ከዓረብ እና ከአፍሪካ እየፈለጉ በማሟላት ወደ ኋላ ተንደርድረው ወደፊት ተፈትልከዋል፡፡ እኛም ዛሬ እንራመድበታለን ብለን ለምናስበው የሥልጣኔ ጎዳና መንደርደርያዎቻችን እነዚሁ መጻሕፍት እና መዛግብት በመሆናቸው ተዘርፈው ከማለቃቸው በፊት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃልም ተናጋሪ ሆነን ልንነሣ ይገባል፡፡ ዛሬ አንዱ ሲሰረቅ ዝም ካልን እየደጋገሙ እንዲዘርፉ ፈቅደናል ማለት ነው፡፡
3

ሕጉ ከ 25 ዓመት በፊት የተጻፉ መንግሥታዊ እና ድርጅታዊ መዛግብት እንደ ጥንታውያን ጽሑፎች ተቆጥረው ወደ ኤጀንሲው እንዲላኩ እንደሚያዝ ሰምቻለሁ

dkibret@gmail.com

:Y¬ãC yÄNx@L :Y¬ãC Daniel kibret’s Views www.danielkibret.com
አንድ ተሰብሳቢ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ «ሰውዬው ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ዳዊት ሰረቀ፡፡ ካህናቱ አዝነው ዝም አሉ፡፡ አላወቁብኝም መስሎት በድጋሚ ሊሰርቅ መጣ፡፡ ያን ጊዜ ቄሰ ገበዙ «አያ እገሌ ዳዊት ልትደግም መጣህ እንዴ? አሉት ይባላል፡፡»

dkibret@gmail.com…...

Similar Documents

Premium Essay

Impact of Technology

...of a highly technological culture, we all use technologies as a part of our daily lives. These technologies are often taken for granted. Some students talk endlessly about a new video game or how they “can't live without” their cell phone or MP3 player. In our society, many people have embraced the benefits of high-technology without considering the possible negative effects of relying too much on these devices. In this assignment, you will have the opportunity to reflect upon the role technology plays in your life and examine how you feel about its effects on your life and the world around you. Requirements Write a report that is approximately 500 – 600 words (two word-processed, double-spaced pages) and outlines the significant interactions that you have had with technology during your life. Autobiographies are usually written in chronological order, but you may use other structures such as flashback or flash-forward if they make sense for your story. Also, because autobiographies typically use first-person, you can use “I” in your paper. To begin, you should take five or ten minutes and brainstorm a list of the technologies that you currently use or have used in the past. It may help to consider the following questions: What technology do you have in your backpack or locker? What technology do you see in the classroom? What technology do you see in other classrooms and locations in the school? What technology do you see in the workplace (yours, a......

Words: 351 - Pages: 2

Premium Essay

The Impact of Technology

...The impact of technology Here are some statistics for you:  More people currently have a mobile phone capable of accessing the internet than have a PC with net access (source: Mobile Top Level Domain, the organisation charged with overseeing the ‘.mobi’ domain name registration)  Sending text messages is now almost as common as talking on mobile phones  Only 12% of mobile users never use their phone for texting (and virtually half of these people are over 65).  70% of 15-24 year-olds say they ‘could not live’ without their mobile phone  There are an estimated 110 million-150 million blogs in existence (although many of these are abandoned soon after they are established) Technology’s role in our lives is astonishing. Its effect on the way we communicate has changed the English language forever. To be more specific, the way we speak today is, by and large, the way we spoke before the internet became what it is, albeit with an enriched vocabulary. Conventions of telephone conversations have, to my mind, changed little: we still use the same methods – if not words – to greet and sign off, for example. What is hugely different, however, is the way we write today. That is the area where technology has had the biggest impact. Email altered the structure of the letter as a communicative tool. It brought with it a whole new etiquette, as well as new conventions and new abbreviations, such as IMO (in my opinion), FWIW (for what it’s worth), IIRC (if I remember......

Words: 310 - Pages: 2

Premium Essay

Impact of Technology

...course of the last decade; arguably as a direct result of technology. We are constantly reminded of the technological advances when attempting to complete the simplest of everyday tasks, viewing entertainment, and all other various forms of entertainment. Nearly everything we do on a daily basis requires some form of technology; cell phones, emailing, vehicles, computers, even schools are all the result of technological advancements that would not have been possible without the significant strides that have been taken in both the business and scientific worlds’. Understanding that technology carries such significance in our lives, can we fathom even just one day without any form of technology? For any business, technology impacts internal and external users alike; companies should take heed to view any new technology they want to implement from all aspects. The company should conduct research to ensure any technological changes will ultimately benefit their customers, employees, and potential customers. One of the most important things to do as a business owner is to ensure that all updated technology is done so in such a way that is conducive to new and repeat business; by maintaining customer awareness, this will aid in the IT team developing the most beneficial technological advances while also discovering new ideas for improvement. * A business should introduce a new product to customers using technology. Technology gives individuals the ability to gain experience......

Words: 1514 - Pages: 7

Premium Essay

Technology Impact

...Technology Impact John Doe TEC/401 January 8, 2013 Technology Impact The impact of technology on customers is huge in regard to customer satisfaction. Technology allows companies to operate more efficiently that increases the productivity and profit of companies. The technology of this time will meet the demands of the customers and allow businesses to expand as necessary. More consumers are smart enough to know the advantages of technology in society. The customers prefer to use the technology to conduct business or complete transactions more quickly. Companies that understand the need for current technology is more likely to remain relevant for years to come. Customers give businesses the keys of success by what he or she requests for businesses. The smarter businesses meet the demands of the consumers while catering to the needs of the target customers. The reluctance to advance technology of some companies can lead to a decrease in profits that may cost the business to collapse. More businesses are advancing technology to remain current and compete with other companies. The ongoing demand for change constantly forces business managers to analyze the need for technology upgrades. Marketing goods and services via the Internet is the most dominant form of promotion for most companies. Most consumers own computers or work with them daily. The familiarity of companies by consumers has made the advancement of technology in companies inevitable. The consumers know what......

Words: 1443 - Pages: 6

Premium Essay

Impact of Technology on Social Interaction

...The Impact of Technology Have you ever looked around and noticed that most people are not paying attention to what they are doing or whom they are talking too? With technology constantly changing it is becoming a major part of our lives and is having both a positive and negative impact on social interaction amongst people of all ages. Technology has changed dramatically and more and more people are relying on it to on a day to day basis. People, especially children went from going outdoors to hang out with friends to communicating by text, Facebook and Twitter. Communicating electronically has been made so user friendly that teens are less interested in face-to-face communication with their friends or family. According to the Telus and Technology survey done in August 2009, shows information and communication technologies are not replacing face-to-face contact but adding or enhancing it. It is giving people the ability to go their separate ways and still stay connected. Families are adding more activities to their daily schedules that text and cell phones are the main line of communication. Another study done by Pew Internet and American life Project shows that 64 percent of adults feel that new technologies has not increased or decreased the how close the family is. Dating has also had an impact of how we interact with people. Before technology, a person would have to gather the courage to go up to someone and say “Hello”, and now with just a few strokes on the......

Words: 619 - Pages: 3

Premium Essay

Impact of Technologies on Teenagers

...The Impact of Technologies on Teenagers An Assignment Submitted by Name of Student Name of Establishment Class XXXX, Section XXXX, Spring 2013 Nowadays, information technologies play a significant role in the modern world. Information technologies have a long history. Some technologies were created a few years ago, while some technologies are comparatively new. Technologies have penetrated all spheres of human activities: education, politics, trade, medicine, and this list can be prolonged. Television and phones are considered to be the primary technologies which appeared in the life of human beings. New technologies were produces in great amounts. Nonetheless, people used those technologies to simplify the process of fulfilling domestic duties. T. K. Derry et. al. mentioned that “domestic housing, though it followed on the whole traditional forms, made use of new materials and new techniques of mass production” (Derry et. al., 1961, p. 403). With further development of information technologies, many other technologies appeared. The main of them are the following ones: iPhones, iPads, and many others. Technologies have produced a great impact on teenagers: phones, television, Internet, and video games have many advantages and disadvantages; they are able to make people technologically informed, but they produce a negative impact on people’s health simultaneously. The invention of mobile phones has produced a great impact on people all over the world:...

Words: 1700 - Pages: 7

Premium Essay

Touchscreen Technology and Its Impact on Society

...Abstract 5 A brief description of the technology and an explanation of the associated science 6 I. Communicating with a network 7 II. Basic idea of the technology 8 III. Breakdown of technology over the past decade 9 The historical development and context of touch or sensor technology 10 I. A historical time line 11 II. The Electronic Sackbut 11 III. PLATO IV Touch-Screen Terminal 12 a. E.A Johnson Touch Screen 12 IV. First Multi-touch Device 13 a. Video Place 13 b. First Multi-touch Screen 13 c. Apple Desktop Bus 13 d. Simon Personal Communicator Phone 14 e. Finger works 14 V. Today’s Touch Screens 15 a. Lemur 15 b. TactaPad 16 c. I Phone 16 d. IPod 16 e. Tablets 16 Political and legal influences 21 i. Political a. Political Applications and Influence (Propaganda) 21 b. Information Sharing 22 c. Data Indexing Routine and Behavior (Personnel tracking & behavior patterns) 23 d. Taxation, new realm of taxes for mobile content and connection 24 e. Government regulations and guidelines 25 ii. Legal Influences a. Privacy concerns and laws 26 b. Data security and encryption 27 c. New laws to deter tax evasion......

Words: 784 - Pages: 4

Premium Essay

Impact of Technology in an Organization

...Introduction Technology has left its magical touch everywhere. Business organizations are not out of that magical touch. Organization development and technology are very closely related. Every organization leverages technology to support their overall strategy. Different organizations are using technology to a various extent. By using technology, organizations have become more efficient than organizations before them. Technology allows the organization to achieve their goals. Technological developments enable productivity allowing reorganization of organizational structure, activities and culture. In return, it greatly improves the effectiveness of the organization. However, for this to last and stay a reality, the use of technology should be leveraged at its fullest extent to maximize results. Indeed, the rise in productivity could be a result of organizations having the ability to grasp, appreciate and absorb current technological advances into their structure, creation and culture. Efficient business processes enable business ventures to save money and time. To hold market share, organizations also try to incorporate the latest technologies as much as possible. Organizations should continue to strive to use modern systems that are concurrent with the latest technological advancement. Therefore, regulating modern systems confirms that organizations consistently use up-to-date technological systems to improve business procedures, as well as ensures that those systems......

Words: 2299 - Pages: 10

Premium Essay

Impact of Technology

...study the impact of information technology and artificial intelligence on the organization, privacy and control, research and instructional practices and ethics. Evolution of information technology has affected all these practices, and has helped them in improving their performance in some way. Information technology has opened a new era of information for today's organization (it might be business, non-profit, educational, research etc.) and has enabled it to gather and communicate information and thus function in a more effective way. On the other hand decision-making capability of the computers has changed the pattern of authority and responsibility with in the organization. Although information technology has bombarded the organization with all kind of information, but it has failed to take into account the limited capability of the society to absorb and use all the available information. In order to make information technology more effective, it must have the capability of providing the organization with relevant information and should be able to realize the needs of the users instead of procedures. Along with providing information, information technology has given rise to various technological problems, like establishing rules to use the available information and protecting it to be accesses by undesirable people. Another thing that the organization needs to be aware about, is the quality of information in order to make quality decisions. Information technology......

Words: 481 - Pages: 2

Premium Essay

Impact Information Technology

...EXECUTIVE SUMMARY Information technology is an amalgam of some wonderful inventions of the 20th century in electronics and communication. During a very short span of time it has acquired an important place in almost all aspects of human life and is found everywhere these days. For most of us, it is hard to image daily life without the influence of technological devices, be it handheld video games, personal digital assistants, cell phones or any number of computers. Through this paper the study on “IMPACT OF INFORMATION TECHNOLOGY” on students and at work place and also the satisfaction level of using IT by these two groups of people have been shown, the advantages and disadvantages of IT. This paper also reflects the problems faced by the students and the employees working in the organization. The objectives of this paper are: • To study the impact of information technology on Students, at work place and on general public. • To study the satisfaction level of using information technology. • To study the problems faced by them. In the research methodology I have taken both primary data as well as secondary data. In the primary data I have made a questionnaire to find out the impact of information technology. In the secondary data I have collected the information from different age groups respondents, from various reports and journals published by different authors and from reports of various study group or working groups appointed by Government from time to......

Words: 7224 - Pages: 29

Premium Essay

Impacts of Advancing Technology on Society

...ABSTRACT Technology is developed to aid society in various ways. As time progresses so do advancements in technology. Technology has become mobile enough through smartphones and tablets that accessing the Internet and other applications instantly have become the norm. As these conveniences become expected by society there will be positive and negative impacts on the individual users. Keywords: smartphones impact society, advancing technology impact Technological advancements increase convenience for society. Computers allow users to keep data organized and available through various programs and the Internet. The launch of handheld, mobile devices such as smartphones and tablets allow users to have instant access to these conveniences from anywhere. Though conveniences are often thought to have a positive impact on an individual’s life, sometimes they can take away essential skills or processes in everyday life that can be beneficial if the technology fails. Mobile technology obviously has its positives, if it didn’t it’s popularity would not be increasing as rapidly as it is. Technology in general helps to keep people better organized. Mobile technology can take it a step further in the fact that the user’s information will always be available to view or update. Advancing technology also offers the ability to sync all devices together so that the users information can be typed into one electronic and transferred to all the others. Another positive aspect......

Words: 1045 - Pages: 5

Premium Essay

Impact of Technology

...instructional technology. Teaching, learning, and computing report, report 8. Retrieved February 25, 2008, from http://​www.​crito.​uci.​edu/​tlc/​findings/​report_​8/​startpage.​htm Apple Classrooms of Tomorrow (ACOT). (2000) Influences and barriers to the adoption of instructional technology. In Proceedings of the mid-south instructional technology conference. Retrieved April, 20, 2008, from http://​www.​mtsu.​edu/​%7Eitconf/​proceed00.​htm Van Dusen, J. (2000) Integrating technology into the classroom: eight keys to success. J Technol Teach Educ 10(1):95–100 Perkins, L. (2001) Putting the pieces together. Paper presented at the international conference on learning with technology, does technology make a difference? Temple University, Philadelphia, March 2000 Erickson, N. (2002) Combining universal access with faculty development and academic facilities. Commun ACM 41(1):36–41. doi:10.​1145/​268092.​268106 CrossRef Roblyer, L. (2007) Oversold and underused: computers in the classroom. Harvard University Press, Cambridge, MA 1. Glyn, P. (Winter 2005) High access and low use of technologies in high school classrooms: explaining an apparent paradox. Am Educ Res J 2. Debard R, Guidera S (2000) Adapting asynchronous communication to meet the seven principles of effective teaching. J Educ Technol Syst 28(3):219–230. doi:10.​2190/​W1U9-CB67-59W0-74LH CrossRef 3. Dede C (2000) Rethinking how to invest in technology. In: Pea Roy D (ed) Technology and......

Words: 1283 - Pages: 6

Premium Essay

Impacts of Technology

...  Today there are over 7.2 billion people on our planet and that number is increasing at an alarming rate. With advances in modern technology our population numbers have seen tremendous results. Doctors today are much more capable of preventing still born and infant deaths and have even made outstanding progress in in-vitro fertilization and other fertility drugs; giving many women the chance to carry children of their own where it would otherwise be deemed impossible if done so naturally. On the other end of the spectrum, doctors are now able to prolong life adding nearly 30 years to our life expectancy. With the human population expected to reach 8 billion people by 2024, can our planet actually sustain that many people? During the Industrial Revolution in the eighteenth century, population numbers began to rise hitting the 1 billion mark in the early 1800’s and has spiraled from there; hitting 2 billion in 1927, 3 billion in 1960, 4 billion 14 years later (1927), 13 years later in 1987 reaching 5 billion, 12 years after we were at 6 billion in 1999, and recently in 2011 we reached the 7 billion mark ("World population," n.d.). We as the human race are reproducing and staying alive much longer and with no sign of it slowing down any time soon. During the 20th century alone, the population of the earth has grown from 1.65 billion to 6 billion people. In 1970, there were roughly half as many people in the world as there are today. ("World population," n.d.). The Peoples......

Words: 1313 - Pages: 6

Premium Essay

The Impact of Technology

...Technology has certainly changed the way we live today. It has impacted different facets of life and redefined living. Undoubtedly, technology plays an important role in every sphere of life. Several mundane manual tasks can be automated, thanks to technology. Also, many complex and critical processes can be carried out with ease and greater efficiency with the help of modern technology. Thanks to the application of technology, living has changed and it has changed for better. These are the things in life we could do faster thank to technology. Technology's Impact on Education has easy access to information, greater interest in learning, increased retention of information, and technology made a huge impacts on kids,teachers,nurses,doctors, and e.t.c. Thanks to techmology its easier for the people. Technology Is A Teaching Aid Computers offer an interactive audio-visual medium. PowerPoint presentations and animation software can be used to present information in an interactive way. Owing to the audio-visual effects, this way of teaching invites greater interest from students. The method is equally helpful for teachers. Projectors and screens facilitate simultaneous viewing of information by a large number of students. Addressing systems using microphones and speakers make it possible for teachers to reach a larger number of students simultaneously. These teaching aids have led to improvements in student attendance and their attentiveness in class. Interactive media have......

Words: 777 - Pages: 4

Premium Essay

Technology Impact

...Technology’s Impact on Employee Training Introduction Technology impacts every aspect of our lives in the 21st century. In our fast-paced professional environments, we continually seek efficiencies with our time management skills and training methods that meet the real time needs of both the organization and the individuals that require that these learning objectives are implemented into their daily jobs. In the past, on-the-job training offered the most effective avenue for transferring knowledge. However, with the introduction of technology in the United States during the 20th century, ensuring quality standards were implemented meant that organizations had to re-evaluate their training methodologies. Additionally, laws implemented to advocate for workers also brought about changes in the approach to employee training. With the onset of technology as a helpmeet for understanding the needs of an organization as well as offering training that helps grow the business, employers began implementing these new technological learning opportunities when offering employees both company-centric and legally required training. Noe (2010) tell us that, “Recognizing the value of human, social, and structural knowledge, many companies are attempting to become learning organizations and to manage knowledge in order to develop better products and improve customer service.” Therefore, as companies proceed into the 21st century and modify their approach to training on a global......

Words: 2491 - Pages: 10